News

Previous Next

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ህብረት ተመሰረተ

በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳድር ደረጃ የሚገኙ 12 የዳያስፖራ ማህበራትን ያካተተ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ህብረት ተመሰረተ።
የምስረታ ስነ ስርዓቱን የከፈቱት የዕለቱ የክብር እንግዳና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብትቱካን አያኖ ባስተላለፉት መልዕክት ዳያስፖራው ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍና ለልዩ ልዩ ሃጋራዊ ጥሪዎች እያደረገ ላለውን ድጋፍ አመስግነው፣ ማህበራቱ አዲሱን ጥላ ማህበበር ተጠቅመው ለበለጠ ስኬታማነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ለጥምረቱ ዕውን መሆን ሂደቱን በመደገፍ ላይ ላለው ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲና ለአደራጅ ኮሚቴው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመቀጠልም በአደራጅ ኮሚቴው የተዘጋጀውና በማህበራቱ አስተያየት የዳበረው ረቂቅ የህብረቱ መተዳደሪያ ደንብ የቀረበ ሲሆን፣ በተሳታፊዎች የማዳበሪያ ሃሳቦች ቀርበውበት ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
በዕለቱም ህብረቱን እንዲመሩ አምስት የስራ አስፈጻሚዎችና ሶስት የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት መድረኩ ሲጠቃለል ባስተላለፉት መልዕክትም ህብረቱ በተሳካ ሁኔታ በመመስረቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ከዚህ በኋላም ኤጀንሲው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል፡፡