News

Previous Next

በውጭ የሚሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በችግር ውስጥ ሆነውም ሃገራቸው ኮቪድ-19ን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት በማገዝ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

በውጭ የሚሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝና ስራ አጥነት በችግር ውስጥ ሆነውም ሃገራቸው ኮቪድ-19ን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት በማገዝ ላይ መሆናቸውን የቱርክ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘገበ።

ዘገባው አብዛኞቹ በቱርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቅሶ፣ በሃገራቸው የኮሮና ቫይረስ ያስከተለውን ጉዳት ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከ3000 ዶላር በላይ በማዋጣት ተምሳሌታዊ ተግባር ማከናወናቸውን ከመግለጹም በላይ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉትን እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህል ለማሳየት ሞክሯል። በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ተመስገንም ድጋፉን ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና በቱርክ የአትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት አባላት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ዘገባው አክሎ ጠቅሷል።