News

Previous Next

ብዛት ያላቸው መንገደኞች በማላዊ በኩል ወደ ሞዛምቢክ ሲጓዙ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተሰማ፡፡

ሕይወታቸው ካለፈው መካከል ኢትዮጵያውያን ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚገመት ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሞቱትን ሰዎች ማንነት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለማጣራት ከሞዛምቢክ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት በመሥራት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

 

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በተከሰተው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ፣ የሞቱት ነፍስ ዘላለማዊ እረፍት እንዲያገኝ ይመኛል።