News

Previous Next

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲና የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችና ማህበራት እንዲሁም የፌዴራል ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

 

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ሰርሚሶ ሳሙኤል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት  ያስተላለፉ ሲሆን፣ ከተማዋ ሁልጊዜም የዳያስፖራ ኢንቨስተሮችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር / ሰላማዊት ዳዊትም በመክፈቻ ንግግራቸው ተሳታፊዎች መድረኩን አክብረው ከልዩ ልዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በመምጣታቸው ምስጋናቸውን አቅርበው በተጠናቀቀው መንፈቅ አመት ኤጀንሲው ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስራዎች አንስተዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም መድረኩ የባለድርሻ አካላት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚቀርብበት፣ የገጠሙ ችግሮች  የሚፈቱበት ሁኔታ በጋራ  የሚለበትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት በመሆኑ የነቃ ተሳትፎ የሚደረግበት እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ መድረኩን በይፋ ከፍተዋል።

በመድረኩ ባለፋት ስድስት ወራት በባለድርሻ አካላት የተከናወኑ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል። ከዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በተጨማሪ በመድረኩ ላይ የኤጀንሲው 10 አመት ረቂቅ መሪ እቅድም የቀረበ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች መሻሻል አለባቸው ባሏቸው ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን፣ ግልጽ ባልሆኑላቸው ጉዳዮች ላይም ጥያቄዎችን አንስተው በሚመለከታቸው ሃላፊዎች ምላሾች ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር መድረኩን ሲያጠቃልሉ ባስተላለፉት መልዕክት መድረኩ አፈጻጸሞችን ከመገምገም አንጻር ውጤቶች የታዩበት፣ ልዩ ልዩ የማሻሻያ ሃሳቦች የቀረቡበትና መሻሻል የታየበት መሆኑን አንስተው፣ ከመረጃ አያያዝ፣ ንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ ከመቀጠል እንዲሁም በክፍተትነት የተነሱ ሌሎች ጉዳዮችን ማሻሻል ኤጀንሲው ባለድርሻ አካላት ቀጣይ የቤት ስራዎች መሆናቸውን  በማመን ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ባለድርሻ አካላቱ የመድረኩን መጠናቀቀ ተከትሎ ይርጋለም የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪና የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓር እንዲሁም በዳያስፖራ ኢንቬስተር የተቋቋመ የሶፍት ፋብሪካን ጎብኝተዋል።