News

Previous Next

በክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከባሕሬን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ሼኻ ራና ቢንት ኢሳ አል ኻሊፋ ጋር ተወያየ

በኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርትኳን አያኖ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከባሕሬን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ(Under Secretary) ከክብርት / ሼኻ ራና ቢንት ኢሳ አል-ኻሊፋ ጋር መጋቢት 26 ቀን 2012 . በባሕሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሳካ ውይይት አድርጓል።

በዚሁ ወቅት አምባሳደር ብርቱካን የባሕሬን መንግሥት ለልዑካን ቡድኑ አባላት ስላደረገው አቀባበልና መስተንግዶ አመስግነው፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር /አብይ አህመድ በዱባይ እና በአቡዳቢ ከተሞች ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ባካሄዱት ውይይት በተለይም ከባሕሬን ለመጡ ዜጎቻችን ቃል በገቡት መሰረት በባሕሬን ማናማ የቆንስላ ጄኔራል / ቤት የሚከፈትበትንና ውሳኔው የሚፈጸምበትን ሁኔታ የባሕሬን መንግሥት እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

በተጨማሪም በአገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በርካታ ዜጎቻችን የመኖሪያና የስራ ፍቃድ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች እንዲሁም ከባሕሬን ጋር ለመፈራረም የተጀመረው የሠራተኛ ስምሪት የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ፈጥኖ የሚጠናቀቅበትንና የሚፈጸምበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ ጠይቀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዘው የባህሬን መንግስት ለዜጎቻችን መብትና ክብር መጠበቅ እያደረገ ያለውን አመስግነው ይሁን እንጂ በባሕሬን ማናማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እያላቸው የታሰሩ ዜጎቻችን ጉዳይ በትኩረት ታይቶ በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲያገኙ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ክብርት አምባሳደር ብርቱካን ባባሕሬን ውስጥ ያሉ በኢትዮጵያውያን የተመሰረቱ የእምነነት ተቋማትን በተመለከተ ምንም እንኳ ዜጎች የማምለክ መብታቸውን የማይከለከሉ ቢሆንም በአገሪቱ ህግ ተመዝግበው እውቅና እንዲሰጣቸውና የተሻሉ የማምለኪያ ቦታዎች እንዲያገኙ፣ እንዲሁም በባሕሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን ህጻናት የሚማሩበት የኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲከፈት እና የኮሚኒቲ አደረጃጀቶች እውቅና እንዲያገኙ ጠይቀዋል።

በባሕሬን በኩልም ክብርት ሚንስትር ዴኤታዋ የቀረቡ ጥያቄዎችን ትኩረት ሰጥተው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል የገቡ ሲሆን፣ ከአሁን በፊት በባሕሬን በኩል ከአገራችን ጋር ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የቪዛ ማስቀረት ስምምነት ለመፈራረም የቀረበው ጥያቄ ውሳኔው እንዲፋጠንና ባሕሬንን ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ በኢንቬስትመንትና በቱሪዝም ለማስተሳሰር እንደሚፈልገልጸዋል። በባሕሬንና በኢትዮጵያ መካካል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከኩዌት ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::