News

Previous Next

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የጉብኝት አብይ ኮሚቴ አባላት በዝግጅቶች ሂደት ዙሪያ በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ውይይት አደረጉ

ክቡር የኢ.... ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሊ .. ከፌብሩዋሪ 13 እስከ 15 ቀን 2020 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን በተለይ አርብ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2020 በዱባይ ከተማ ሸባብ አልአህሊ ክለብ በአልመክቱም ስታዲያም የሙሉ ቀን ዝግጅት ላይ በመገኘት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና በመካከለኛው ምስራቅ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መልእክት ያስተላልፋሉ።

ይህንኑ ዝግጅት ለማስተባበር ከህብረተሰብ አደረጃጀቶች ከሃይማኖት አባቶችና ከልማት ማህበራት የተውጣጣ አብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል። በተለይ አርብ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2020 ህብረተሰቡ ከሰባቱም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግዛቶች በነቂስ ወጥቶ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርን እንዲቀበልና እንዲገናኝ ለማድረግ እየተከናወኑ ስላሉ እንቅስቃሴዎች እና የቅስቀሳ የመስተንግዶ የሎጀስቲክ ስራዎች የስራ ሂደት በተመለከተ ከክብርት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከወ/ ሰላማዊት ዳዊት እና ከአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክቡር አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ፣ ከክብርት / እየሩሳሌም አምደማሪያም ጋር የካቲት 2ቀን 2012 . በዱባይ የኢ... ቆንስላ ጄኔራል /ቤት ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በዋነኛነት በዜጎች ጉዳይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትና በመካከለኛው ምስራቅ ከሚኖሩ ዜጎች ጋር ለመወያየት የሚመጡ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዓርብ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2020 በዱባይ ሸባብ አል አህሊ ክለብ በአልመክቱም ስታዲየም እንዲገኙ መልዕክት እንዲደርሳቸው ለማድረግ ኮሚቴዎቹ በቀጣይ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ከየግዛቶቹ ወደ ዝግጅት ቦታው ለሚመጡ ዜጎቻችን በየ ግዛቶቹ ከተሞች አማካይ ቦታዎች ነጻ የአውቶቡስ የትራንስፖርት አገልግሎት የተዘጋጀ ሲሆን አውቶቡስ ማቆሚያ ቦታዎች እና አስተባባሪዎችን የተመለከተ መረጃዎች በቀጣይ ለህብረተሰቡ የሚገለጽ ይሆናል።

የዝግጅት ቦታ ዱባይ ሸባብ አህሊ ክለብ አልመክቱም ስታዲየም
ቀን፡ አርብ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2020
ሰዓት፡ በዱባይ ሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ (1100 a.m.
እስከ 500 p.m)
ስታዲየም መግቢያ ሰዓት እስከ ቀኑ 200 PM