የመብት ማስጠበቅና የህግ ከለላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ዜግነታቸውን ያልቀየሩ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደማንኛውም ዜጋ ከመንግስት ሊያገኛቸው የሚገቡ ግልጋሎቶች እና ሊጠበቅላቸው የሚገቡ መብቶች አሏቸው፡፡ የዳያስፖራ ፖሊሲ አንዱ ትልቁ መነሻም ይኼው የመብት እና ጥቅም ማስከበር ጉዳይ ነው፡፡ ኤጀንሲው ከቁልፍ ተግባራቱ አንዱ ይህንን ሲያደርግ በዋነኛነት የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ መብት እና ጥቅም እንዲሁም የሰብአዊ እና ሲቪል መብት እና ጥቅም በሚል በሁለት ንዑስ ክፍሎች በመመደብ ነው፡፡ ዳያስፖራው ከቤተሰባዊ ጉዳዮች ጀምሮ እስከ አካባቢያዊ እና በሚኖርበት ሀገር ጋር የተያዙ ማህበራዊ ጉዳዮቹን በተደራጀና ህግን በተከተለ መልኩ እንዲያከናውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሰብአዊ እና ሲቪል መብቶቸቸውን ማስከበር፣ ከነዚህ ጋር የተያያዙ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማካሄድን ያካትታል፡፡ በዳያስፖራው ውስጥ ካሉ ማህበራዊ አደረጃጀቶች ለምሳሌ እድር እና የሀይማኖት መሰባሰቦችን የማህበረሰቡን ማህበራዊ ደህንነት እንዲያስጠብቁ በመተባበር መስራት፡፡ ከስራ ላይ ደህንነት ጋር የተያያዙ ስራዎችን መስራት፡፡ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ውስጥ በማህበራዊ ጉዳዮች እና በመብት ላይ የሚሰሩ ሲቪክ ማህበራትን ማበረታታ፣ በማህበረሰቡ ውስጥም ትልቅ ሚና እዲወጡ መደገፍ የዚህ የስራ ክፍል ዋና ዋና የሚባሉ ተግባራት ናቸው፡፡