ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19ን) ለመከላከል በሃገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን ሃብት የማሰባሰብ ንቅናቄ መደገፍ ለምትፈልጉ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ! በኮሮና ቫይረስ የተደቀነብንን ፈተና መከላከል እንዲቻል በሃገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የሃብት አሰባሳቢ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ በሃገር ውስጥ የሚገኘውን ሃብት የማሰባሰብ ስራ በማከናወን ላይ ነው ። ከኢትዮጵያ ውጭ ያለውን የሀብት ማሰባሰብ ስራ ደግሞ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በንኡስ ኮሚቴነት እያስተባበረው ይገኛል። በመሆኑም በያላችሁበት ሃገር ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ጋር በመነጋገር የገንዘብም ሆነ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የምትችሉበት ሁኔታ የተመቻቸ ሲሆን፣ በተፈጠረው የጉዞ ዕቀባ ምክንያት ከሚሲዮኖች ጋር ግንኙነት ማድረግ የምትቸገሩ ከሆነ ኢትዮቴሌኮም ባዘጋጀው Ethioremit.com ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ኤጀንሲው!

Image

ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ተገልጋዮች በሙሉ

የተለያዩ አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት የሚያስችሉ ስልቶችን እየዘረጋን ሲሆን፣ ይህንንም ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየሰራንበት እንገኛለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ለተወሰኑ አገልግሎቶች በአማራጭነት የኦንላይን አገልግሎት ጀምረናል።

በመሆኑም:- የኢንቨስትመንት የድጋፍ ደብዳቤ ማጻፍ የምትፈልጉ ዳያስፖራዎች ከኤጀንሲያችን ዌብሳይት www.ethiopiandiasporaagency.org ዳውንሎድ ታብ ውስጥ በመግባትና አስፈላጊ ሰነዶችን በማውረድ ፎርሙን እንድትሞሉና የሞላችሁትን ፎርምና የስልክ ቁጥራችሁን በኢሜይል አድራሻችን diaspora.agency@mfa.gov.et ወይም awlachew.masrie@mfa.gov.et ወይም tesfaye.wolde@mfa.gov.et ወይም melaku.zeleke@mfa.gov.et ወይም tafadadi@gmail.com እንድትልኩ እየጠየቅን፣ ጉዳያችሁ እንዳለቀ በስልክ ቁጥራችሁ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን።

እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር ቀጠሮ እንዲያዝላችሁ የምትፈልጉ

 ቀጠሮ የሚያዝበት መ/ቤት ስም፣
 ጉዳዩ (ቀጠሮ የሚያዝበት ምክንያትና ተያያዥ ሰነዶች) እና
 የስልክ ቁጥራችሁን በመጥቀስ በኢሜይል አድራሻችን diaspora.agency@mfa.gov.et እንድትልኩ እየጠየቅን፣ ጉዳያችሁ እንዳለቀ በስልክ ቁጥራችሁ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን።

ኤጀንሲው

ጠ/ሚ ዐቢይ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያስተላለፉት መልዕክት

እኔ ለሀገሬ፣ ሀገሬም ለእኔ

ዋና ግቦች

የዳያስፖራ ማህበረሰብ ልማት ስራዎች

የዳያስፖራ ማህበረሰብ ልማት ስራዎች

ይህ ስራ ዳያስፖራውን በሚመለከት ለሚሰሩ ማህራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎች እንደ ቅድመ ሁኔታ ሊወሰድ የሚችል ቁልፍ ሚና ነው፡፡
የዳያስፖራ ተሳትፎ ማስፋፋትና ማጠናከር

የዳያስፖራ ተሳትፎ ማስፋፋትና ማጠናከር

የዳያስፖራ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት እስከ አሁን ከነበሩ ተሞክሮዎች እና አሁን ላይ ከሚፈለገው የዳያስፖራው የተሳትፎ አይነትና የወደፊት አስፈልጎት በመነሳት ቁልፍ በሆኑ የተሳትፎ አይነቶች የተደራጀ ነው፡፡
የመረጃ፣ ጥናትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የመረጃ፣ ጥናትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ይህ የስራ ክፍል ዳታ ቤዝ ማደራጀት፣ መረጃ መተንተንና ተወራራሽ የሆኑ ተቋማዊ የመረጃ ክምችት (Institutional memory) እንዲኖር የማድረግ ስራን ይሰራል፡፡
የመብት ማስጠበቅና የህግ ከለላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የመብት ማስጠበቅና የህግ ከለላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ዜግነታቸውን ያልቀየሩ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደማንኛውም ዜጋ ከመንግስት ሊያገኛቸው የሚገቡ ግልጋሎቶች እና ሊጠበቅላቸው የሚገቡ መብቶች አሏቸው፡፡

አዳዲስ ዜናዎች

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስን ለመመከት ለቀረበው ሃገራዊ ጥሪ የገንዘብና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ጀመሩ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎ...
ሕይወታቸው ካለፈው መካከል ኢትዮጵያውያን ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚገመት ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሞቱትን ሰዎች ማንነት እና ተያያዥ...
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችና ማህበራት እንዲሁም የፌዴራል ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ...
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ሁሉንም ሰራተኞቹን ባሳተፈ መልኩ በኤጀንሲው የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች በዳያስፖራ ተሳትፎ ዙሪያ...
  በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራውና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊትን ያካተተው ከፍተኛ የልዑካን...

ኒውስሌተር

Subscribe to get latest updates and events